⭕️Live🛑ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ

⭕️Live🛑ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ

ቅዱስ ጊዮርጊስ፡ የሰማዕታት አለቃና የጽናት ተምሳሌት፦ ​ቅዱስ ጊዮርጊስ "ክርስቲያን ነኝ" ብሎ ራስን ማስተዋወቅ እንደ ትልቅ ወንጀል በሚቆጠርበትና በሞት በሚያስቀጣበት በዚያ በጨለማው የሰማዕታት ዘመን፣ ስለ ክርስቶስ ፍቅር በድፍረት የቆመ ወጣት ነበር። ሰባ ነገሥታት ተሰብስበው አምልኮተ ጣ.. እንዲቀበል ቢያስገድዱትም፣ እርሱ ግን "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየኛል?" በማለት መከራን በትዕግሥት ተቀበለ። ​በገድሉ ላይ እንደተጠቀሰው፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ መከራ እጅግ ዘግናኝ ነበር። ሰማዕቱ አጥንቱ ተፈጭቶ፣ አካሉ እንደ ሰም ቀልጦ በደብረ ይድራስ ተበተነ። ከሰው አዕምሮ በላይ በሆነ ተአምር ግን እግዚአብሔር አምላክ አጥንቱን ሰብስቦ፣ ነፍሱን መልሶ ድጋሚ ለምስክርነት አስነሳው። ​ይህ ብቻ አይደለም፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሕያው መሆኑን ለማረጋገጥ ተፈጥሮም ምስክርነቷን ሰጥታለች። መከራ በሚቀበልበት ወቅት ደረቅ የሆኑ እንጨቶች (ቅጠሎች) በፊቱ እንዲለመልሙ፣ እንዲያብቡና እንዲያፈሩ በማድረግ የጌታችንን የፈጣሪነት ሥልጣን ለከሳሾቹ አሳይቷል። ​ዛሬም ድረስ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽናት ለእኛ ለክርስቲያኖች ትልቅ ትምህርት ነው። መከራ ቢበዛ፣ ዓለም ቢጨልምም በእግዚአብሔር የታመነ እንደማያፍር የሰማዕቱ ታሪክ ሕያው ምስክር ነው። ​የሰማዕቱ አማላጅነት አይለየን⛪️✝️ ​#ደብረ_ይድራስ #ተአምረ_ጊዮርጊስ #ሰማዕትነት #ገድለ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ #ተዋህዶ_ሃይማኖቴ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #StGeorgeTheMartyr #OrthodoxFaith #Ethiopia with CameraFi Live