ኢየሱስ በስጋዉ ወራትና ከዕርገቱ ቦኃላ እንደሚማልድ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡

ኢየሱስ በስጋዉ ወራትና ከዕርገቱ ቦኃላ እንደሚማልድ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡

ኢየሱስ በስጋዉ ወራትና ከዕርገቱ ቦኃላ እንደሚማልድ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ኢየሱስ አማላጅ ነዉ የኢየሱስ ያመካከለኛነቱ ሁለተኛዉ ሥራ አማላጅነቱ ነዉ፡፡ እርሱ በአምላክነቱ ጸሎትንና ምልጃን እንደሚቀበል በሰዉነቱ ደግሞ ስለእኛ ይማልዳል፡፡ ኢየሱስ በስጋዉ ወራትና ከዕርገቱ ቦኃላ እንደሚማልድ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ምልጃዉም አስታራቅነቱንና ጽሎትን ያጠቃልላ፡፡ አሁን የሚናየዉ የምልጃ ጸሎቱን ነዉ፡፡ ሀ/በሥጋዉ ወራት ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ሰይጣን እነጰጥሮስን እንደ ስንደ ሊያበጥራቸዉ ሰይጣን በለመነ ጊዜ አምነቱ እንዳይጠፋ አማልዷል፡፡ ሉቃ 22፡31- 31 ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ 32 እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።-----ስንፈተን እምነታችን እንዳይጠፋ እና ወደሥፍራችን እንድንመለስ ነዉ፡፡ ለብዙ ህዝብ መዳንና ቤተ ክርስቲያን መሥራች ሆነ፡፡ ይህ የምልጃ ዉጤት ነዉ፡፡ But I have prayed for you, that your faith should not fail ዮሐ 17፡9- 9 እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤ 20-21 ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። ሉቃ 23፡34- በመስቀል በነበረ ጊዜ ስለሰቀሉት ሰዎች ማልዷል፡፡ 34 ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። በሥጋዉ ወራት ጌታችን ያቀረበዉ የምልጃ ጸሎት ልክ መሞቱ ለሁላችን እንደሆነ ምልጃዉም ለኛም ጭምር ሆነ፡፡ ዮሐ፡ 17 20-21 ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። ከዕርገቱ ቦኃላ 1. ሮሜ 8፡34 34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። 34 Who is he that condemneth? It is Christ that died, yea rather, that is risen again, who is even at the right hand of God, who also maketh intercession for us. እንግድህ ጌታችን በአብ ቀኝ የተቀመጠዉ ከረገ ቦላ እንደሆነ እናዉቃለን፡፡ 1.ጰጥሮስ 3፡22 እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ። ማርቆስ 16፡19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። 2. ዕብ 7፡25 23 እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ 23 And they truly were many priests, because they were not suffered to continue by reason of death: 24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ 24 But this man, because he continueth ever, hath an unchangeable priesthood. 25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። 25 Wherefore he is able also to save them to the uttermost that come unto God by him, seeing he ever liveth to make intercession for them. 3. ወደ ዕብራውያን 8 Heb 8 1 ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ 1 Now of the things which we have spoken this is the sum: We have such an high priest, who is set on the right hand of the throne of the Majesty in the heavens; 2 እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት።ሳሚ 2 A minister of the sanctuary, and of the true tabernacle, which the Lord pitched, and not man.