የዮሐንስ ወንጌል ክፍል 5 | በስሙ ማመን | | በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን | THE GOSPLE OF JOHN |By Evangelist Yared Tilahun
ይህ ትምህርት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ቁጥር 12 እና 13 ላይ የተመሠረተ ሲሆን በደካማ ሥጋ፣ በተናቀ ማንነት፣ ካልተጠበቀ ስፍራ የመጣውን ጌታ በጊዜው በእስራኤል ከነበሩት አብዛኞቹ እንዳልተቀበሉት ይነግረንና ነገር ግን ጥቂቶችም ቢሆኑ እሱ ክርስቶስ ነው! የእግዚአብሔር ልጅ ነው! ብለው በስሙ (በባሕሪው፣ በማንነቱ፣ በሥራው) ለተቀበሉት የሰጣቸውን ስጦታ ይነግረናል። ስጦታውም በሰማይም ሆነ በምድር፣ በጊዜ ውስጥም ሆነ በዘላለም አቻ የሌለው ትልቅ ስጦታ ነው። ያም ስጦታ ልጅነት ነው። ልጅነት ከስጦታዎች አንዱ አይደለም። ስጦታዎች ሁሉ በልጅነት ውስጥ ናቸውና ልጅነት ሁሉን ወራሽነት ነው። አምነህ/ሽ ልጅ ሆነሃል/ሻል? ከሆንክ/ሽ የልጅነት ዋጋው እጅግ ክቡር መሆኑ ምን ያህል ገብቶሃል/ሻል? መልካም የትምህርት ጊዜ