የዮሐንስ ወንጌል | መግቢያ ክፍል 1| በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን | THE GOSPLE OF JOHN |By Evangelist Yared Tilahun
ይህ የዮሐንስ ወንጌል መግቢያ ነው። በእርግጥ ዮሐንስ ወንጌል የለውም፡) ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው የሚለውን የአበው ቃል ብንጠቀም ይመረጣል። ይህ ወንጌል ከማቴዎስ፣ ከማርቆስ እና ከሉቃስ ወንጌል የተለየ ምልከታ አለው። እነርሱ በኢየሱስ የገሊላ አገልግሎት ላይ ሲያተኩሩ፣ ዮሐንስ ግን በኢየሩሳሌም አገልግሎቱ ላይ ያተኩራል። ይህ ወንጌል በአንድ በኩል ቀላል፣ በሌላ በኩል ግን ጥልቅና ረቂቅ ነው። አብዛኛዎቹ የትምህርተ-ክርስቶስ አስተምህሮዎች የወጡት ከዚህ ወንጌል ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስ ማን እንደ ሆነ ለማወቅና ለምን ሥጋ እንደ ሆነ፣ ለምን በመስቀል ላይ እንደ ሞተና እንደ ተነሳ በሚገባ ለመረዳትና ለማመን፣ አምኖም በእርሱ በኩል የመጣውን የሕይወት ስጦታ ለመቀበልና በዚህም ሕይወት እሱን እየመሰሉ ለመኖር ይህንን መጽሐፍ በጥልቀት ማጥናት የግድ ነው። መልካም የትምህርት ጊዜ!!!